‹‹መገፌ››
‹‹መገፌ››
በአንዳንድ የአገራችን ከተሞች ላይ በተለይ በጅጅጋና በነጌሌ ቦረና አካባቢ ባጃጆች ‹‹መገፌ›› በሚል ቅፅል ስም እየታወቁ ነው፡፡
ያለንበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር (ስደት) ያለበት የአለማችን ክፍል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለዚህም የቀጠናው ሰላም ማጣትና ደህነት በዋናነት እንደምክንያት ቢጠቀሱም የተሻለ ኑሮን እናገኛለን በሚል ቀቢፀ-ተስፋ የሚደረጉ ስደቶችም ቀላል የማይባል ሚና አላቸው፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚያመቻቹ አካላት ከወትሮ በተለየ መልኩ የተደራጀ የአሰራር መረብ ዘርግተው ገበያቸውን እያጧጧፉት ይገኛሉ፡፡ በተለይ ጨቅላ ወጣቶችን ውጭ (አውሮፓ አገር) እንልካቿለን ብሎ እየሰበኩ ከማማለል እስከ ማስኮብለል የሚሰራ መዋቅር እንዳለው የሚነገርለት ‹‹መገፌ›› የሚባለው ቱባ የአዘዋዋሪ መረብ በቀጠናው ጠንካራ ተቋም እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ከጅጅጋ አንስቶ እስከ ጣሊያኗ ላምፖርቶ ወደብ ድረስ የተዘረጋ መረብ እንዳለው ይነገራል፡፡ ‹መገፌ› የዚህ መረብ ዋና አንቀሳቃሽ መቀመጫውን ሊቢያ ያደረገ ሱማሊያዊ ሰው ስም እንደሆነም ይነገራል፡፡
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በርካታ ታዳጊ ወጣቶችን እያስኮበለለ ያለው ይህ ተቋም በአጭር ግዜ ውስጥ ከአዲስ አበባ በሱዳን አድርጎ ሊቢያ ድረስ የሚያደርስ የዝውውር መረብ እንዳለውና ይህን ጉዞ ለማድረግም ምናልባትም ወጪውን እራሱ የሚሸፍንበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች ይነገራል፡፡ ሊቢያ ካደረሰ በሗላም ለተጓዦቹ ስልክ በማስደወል ከቤተሰባቸው ከ100 ሺ እስከ 150 ሺ ብር እንዲያስልኩ ያመቻቻል፡፡ ያ ካልሆነ አንድ ኩላሊታቸውን እንደሚወስደው ያስጠነቅቃል፡፡ ይህን የሰሙ ቤተሰቦች የጨቅላ ልጃቸውን ህይወት ለመታደግ ፤ተበድረው፤ ለምነው፤ ወይም ንብረታቸውምን ቢሆን ሸጠው ‹ላኩ› ወደተባሉት ( ሱዳን) ባንክ ይልካሉ፡፡ ይህ መረብ በዚህ መልኩ በርካታ ታዳጊ ወጣቶችን ከአገርና ከቤተሰብ አስያስኮበለለ በታዳጊዎችና ቤተሰቦቻቸው ላይ ችግር እየሆነ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በጣት የሚቆጠሩ ወጣቶች በዚህ መረብ ተጉዘው ጣሊያን ቢገቡም አብዛኞቹ ገንዘብ ከተላከላቸው በሗላም እንዳልተሳካላቸውና ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉ ይነገራል፡፡ በዚህ ወጥመድ ውስጥ በቀሩባቸው ልጆቻቸው ሃሳብ ብቻ ለበሽታ የተጋለጡ ወላጆችም አሉ፡፡
ታዲያ አንዳንድ ፍንዳታ ታዳጊዎች ባጃጅ ካልተገዛልን እንደ ኤገሌ ልጅ መገፌ ጋር እንሄዳለን ብለው ቤተሰባቸውን በማስፈራራት ማስቸገር ጀምረዋል፡፡ ይህን ጦስ ፈርተው ለልጆቻቸው ባጃጅ የገዙ ቤተሰቦችም በርካታ ናቸው፡፡ ለባጃጆች ‹መገፌ› የሚል ቅፅል ስም የተሰጣቸው በዚህ ሰበብ ነው፡፡
እባካቹ ወጣቶች ከራሳቹ ሁኑ፡፡ በዚህ ህገ ወጥ የቀቢፀ- ተስፋ ድርጅት ተታላቹ እራሳቹና ቤተሰባቹ ላይ ጦስ አትሁኑ፡፡